የአብክመ ኀብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን ዋና ኃላፊ መልዕክት

             የኃላፊው መልእክት

ኅብረት ስራ ማህበራት የአባላትን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክልሉ ብሎም በሃገሪቱ ልማትን ለማፋጠን፣ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ዴሞክራሲን ለማስፈንና የሃገር ዕድገት ለማስቀጠል ቁልፍ ተልዕኮ ተሰጧቸው ከሚንቀሳቀሱት ተቋማት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ድህንነትን ለመቀነስና የህብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል ወደ ዘመናዊ ግብርና ልማት ለመቀየር የተነደፈውን የገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ ዕውን ለማድረግ፣ ኅብረት ስራ ማህበራት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን፣ የፍጆታ ዕቃዎችንና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን ወደ አርሶአደሩ መንደር በሚፈለገው አይነት፣ መጠን፣ ጊዜና ቦታ በማቅረብና የአረሶአደሩን የመደራደር አቅም በማሳደግ ረገድ በማንም የማይተካ ሚና እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

በክልላችን በርካታ ዘርፎች የልማት አንቀሳቃሽ ሞተር የሆነው የኀብረት ስራ ማህበራት በእስካሁኑ ጉዞው ለአባላት ተጠቃሚነትና ኑሮ መሻሻል እና ሃገራዊ ሁሉን አቀፍዕድገት ያስመዘገባቸው ውጤቶች በቀጣይም የዕድገት ጉዛችን ስኬት የኀብረት ስራ ማህበራት ሪፎርም እንደሃዲድ ሆኖ እንዲያገለግ ልይታመናል፡

ዘርፉን ለማጠናከር በተሰሩ ዘርፈብዙ ስራዎች በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡  በግብርናነክ ፣ ግብርናነክ ያልሆኑ፣ የሸማቾች፣ በገንዘብ ቁጠባና ብድር 9532 እንዲሁም በመኖሪያ ቤት ከ20389 መሰረታዊ ኀብረት ስራ ማህበራት ፣ 76 ዩኒዬኖችና 1  የኀብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ፌደሬሽን በተለያዩ ዘርፎች ተደራጅተው ባለፉት ዓመታት ኅብረት ሥራ ማህበራት የግብርና ግብዓቶችና ቴክኖሎጂዎች በማቅረብ፣ ለአርሶና አርብቶ አደሩ ምርቶች የገበያ ትስሰር በመፍጠር፣ በከተሞች የሚታየውን የምርትና ሸቀጥ የዋጋ ውድነት በማቃለል፣ አግሮፕሮሰሲንግ በማቋቋም፣ የቁጠባ ባህል በማሳደግና የስራ እድል በመፍጠር ለአባሎቻቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መዋቅራ ዊሽግግር ለማድረግ በክልል ከሚገኙ 20 የሚሆኑ ዩኒያኖች እና 3 መሰረታዊ ማህበራት በዱቄት፣ በመኖ ማቀነባበር፣ በዘይት መጭመቅ፣ በማር ማቀነባበርና ማጣራት፣ በምጥን ማዳበሪያ ማቀነባበር፣ በወተት ማቀነባበር፣ በሳሙና ማምረት እና የግብዓት መያዣና የምንጣፍ ማምረት ተግባር የተሰማሩ ሲሆን በአብዛኛዉ በወተት ልማትና ግብይትና ማቀነባበር የተሰማሩትን ጨምሮ ደግሞ ከ178 በላይ መሰረታዊ የኅብረት ስራ ማኅበራት በተለያዩ አነስተኛ አግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ተሰማርተዉ የአባሎቻቸዉን ምርት በመረከብና እሴት በመጨመር አርሶአደሩ የድካሙ ቀጥተኛና ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡የግብርናውንክፍለኢኮኖሚበማዘመንምርትናምርታመናትንለማሳድግበሚፈፀሙተግባራትዩኒያኖችእናበመሰረታዊህብረትስራማህበራትትራክተሮች  ፣ኮምባይነሮች፣ እና አነስተኛ የስንዴ መውቂያ ትሬሸሮችን በመግዛት ወደ ስራ በማስገባት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

የኅብረት ሥራ ማኅበራቱን በአገራችን ማደራጀት ከተጀመረ ከ60 ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም አባላትን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ለአገራዊ እድገቱ ያደረጉት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገት አስተዋፅኦ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተቋማቱ የሚጠበቀውን ያህል ነው ብሎ መናገር አያስደፍንም፡፡ወቅቱ የሚጠይቀውን የአሰራር፣ የአመራር፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ዘመናዊነትን ተላብሶ የአባላትን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጥያቄዎች ከመመለስ አኳያ አሁንም ችግር እንደሆነባቸው ይታያል፡፡የዚህ ችግር መሰረታዊ መንስኤዎች በርካታ ቢሆኑም የኅብረት ስራ ማኅበራቱን ከማቋቋም ጀምሮ በየደረጃዉ ተገቢ ድጋፍ እያደረጉ እንዲጠናከሩ ከማድረግ ዘመኑን የዋጀ አሰራርና አመራር እንዲከተሉ ያሉባቸውን ክፍተቶች በመለየት ለክፍተቱ የሚመጥን መፍትሔ እያስቀመጡና እየተገበሩ አለመሄድ ዋነኛው ችግር ነው፡፡

ሪፎርሙን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከፊታችን በርካታ የቤት ስራዎች እንደሚጠብቁን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ የኅብረት ስራ ማኅበራትን የማዘመንና ሪፎርም የማድረግ ስራ ለነገ የማይባልና የማይታለፍ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡እንደ ኀብረታችን ወንድማማችነታችን፣ ትስስራችን፣ አብሮነታችን፣ አንድነታችንና አቃፊነታችን የመላው ኀብረት ስራ ማህበራት አባላትና ቤተሰቦቻቸውን ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዛችን እውን ለማድረግ ብዙሁነን እንደ አንድ፤ አንድሁነን እንደ ብዙ ለሪፎርሙ እናሁለንተና ዊስራዎቻችን በጋራ መቆም ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል በሚሰሩ ስራዎች የክልላችን ህዝብና መንግስት እንዲሁም ባለድርሻ እና አጋር አካላት የተለመደ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡ 

ኀብረት ስራ ማህበራት ከማደራጀት ባሻገር!

አቶ ጌትነት አማረ

የአብክመ ኀብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን ዋና ኃላፊ

ስለ ባለስልጣኑ

  • sss

  • Sed ut perspiciatis unde omnis iste natus error sit voluptatem, totam rem aperiam, eaque ipsa quae ab illo inventore et quasi architecto beatae vitae dicta sunt explicabo.

ራዕይ

የክልላችን ህብረት ስራ ማህበራት እንቅስቃሴ ጎልብቶ ዝላቂና ጠንካራ የኢኮኖሚ መሰረት ያለዉና በራሱ የሚተማመን ህብረተሰብ በ2022 ዓ.ም ተፈጥሮ ማየት።

የክልላችን ህዝብ ያለውን ሀብት መሰረት ብማድረግ፣ በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ፣  ነፃና ዴሞክራሲያዊ  በሆነ አደረጃጀትና አመራር፣ የተለያየ አይነትና ደረጃ ያላቸው የህብረት ስራ ማህበራትን ማደራጀት፣ አቅምን ማሳደግ፣ ዘመናዊ የመረጃ፣ የሂሳብ አያያዝ ስርዓትን በመዘርጋት የህብረት ስራ ማህበራት በህግና ደንብ ተመርተዉ  ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን በጋራ በመፍታት ተጠቃሚ እንዲሆኑ  ለማድረግ።

  • ግልጽነት
  • ተጠያቂነት
  • ፍትሃዊነትና አሳታፊነት
  • ታማኝነት
  • ቁርጠኝነት
  • መተባበር
  • በራስ መተማመን
  • አባልነት በፈቃደኝነት የተመሰረተና ለሁሉም ክፍት በመሆኑ
  • አባላት በዲሞክራሲያዊ አመራርና ቁጥጥር ይመራሉ
  • በአባላት ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ላይ የተመሰረቱ መሆናቸዉ
  • ራስ ገዝና  እራሳቸውን በራሳቸዉ ማስተዳደሩ መሆናቸው
  • ትምህርት, ስልጠናና እና መረጃ  መስጠት
  • ከሌሎች አቻ ህብረት ስራ ማህበራት ጋር ህብረት መፍጠር
  • ማህበራዊ ሃላፊነት, ለአካባቢያዊ ዘላቂነት ጥረት ማድረግ

በሀገራችንም ሆነ በክልላችን የኀብረት ስራ እንቅስቃሴ በአጼው የተጀመረቢሆንም እንደ ሶስትኛ የታሪክ ምዕራፍ የሚታየው ከግንቦት 1983 በኋላ ያለው ጊዜ ሲሆን፣ ለዚህ ዘርፍ በቅድሚያ የኢፌዴሪ መንግስት ጥር 24 ቀን 1986 ዓ/ም ያወጣው የገበሬዎች ኀብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 85/86 በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ ዓለም አቀፍ የኀብረት ሥራ መርሆችን መሰረት በማድረግ የሕብረት ሥራ እንቅስቃሴ ትክክለኛውን ትንሳኤ ለማግኘትና፣ ለእስካሁኑ ሂደት በር ሊከፍትችሏል፡፡

ይሁን እንጅ ከ1986 በኋላ በነበረ ውሂደት የኅብረት ሥራ ማኅበራቱ የአባላቱንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ ይቻል ዘንድ በመንግስት የልማት ፖሊሲ ትኩረት ያገኙ ቢሆንም የሚጠበቀውን ያህል እድገትና አስተዋፅኦ ሊያመጡ ስላልቻሉ የህብረት ስራ ማህበራቱን አለም አቀፍፋዊና ሃገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ግምት ዉሥጥ ያስገባ ቀደም ብሎ የወጣዉን አዋጁን እንደገና ማሻሻል አስፈልጓል፡፡የኢፌዲሪ መንግስት ለዘርፉ ልማት በሰጠው ልዩት ኩረት ሁሉንም የኅብረት ስራ ማኅበራት ዓይነት እና ደረጃ ያካተተ ሆኖ የወጣው የኅብረት ሥራ አዋጅ ቁጥር 147/91 ለሃገራችን የሕብረት ሥራ እንቅስቃሴ ከመቸውም የበለጠና የተሻለ የሕግ መሠረትና ድጋፍ ያገኘ እርምጃ ተወሰደ፡፡የክልላችን መንግስትም ለዘርፉ በሰጠው ተመሳሳይ ትኩረት በክልሉ የኅብረት ሥራ ማህበራት እንዲቋቋሙ፣ እንዲጠናከሩና ተገቢውን ድጋፍ ከመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲያገኙ በፌደራል አዋጅ ያልተካተቱትን በማካተት አዋጅ ቁጥር 134/1998 እንዲወጣ ተደርጓል:: የኀብረት ስራ ማህበራት የሚመሩበት የነበረውን ችግሮች ሊፈታ በሚችል ቆየት ያሉትን አዋጅ በማሻሻል በክልላችን አዋጅ ቁጥር  220/2007 የወጣሲሆንበፊዴራልደረጃምአዋጅቁጥር 985/2009  እንዲወጣ ተደርጎ እየተተገበረበት ይገኛል፡፡

የአደራጅ ተቋሙ በ1988 በጀት አመት በግብርና ቢሮ ስር የእርሻ ልማትና ኀብረት ስራ ማህበራት ማዳራጃ በሚልበ መምሪያ ደረጃ ስራውን ጀመረ፡፡ከጥቂት ወራት በኃላ በክልል ርዕሠ መስተዳድረ ጽ/ቤት ስር  6  ባለሙያዎች ይዞ ሚያዚያ 1988 የገበሬዎች ኀብረት ስራ ማህበራት ጉዳይ መከታተያ ጽ/ቤት ተብሎ በማደራጀት ስራውን መስራት ቀጠለ፡፡በ1990 ዓ.ም የገበሬዎች ኀብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ጽ/ቤት ተብሎ እራሱን እንዲችል ተደርጎ ከተዋቀረ በኃላ በአመቱ በ1991 ዓ/ም በሶሰት መምሪያዎችና በሁለት አገልግሎቶች ተደራጅቶ በአዋጅ ቁጥር 4ዐ/1991 የተቋቋመው የአማራ ብሄራዊ ክልል የኅብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ቢሮ  ከክልል እስከወረዳ ባሉት እርከኖች በድምሩ 2,851 የሰው ኃይል ይዞ ሲንቀሣቀስ ቆይቷል፡፡የአደራጅ ተቋሙ ስራዉን (1988) ሲጀምር ከደርግ መንግስት በሁለት የስራ መስክ የተሰማሩ 861 የገበሬዎች አገልግሎት መሰረታዊ ኀብረት ስራ ማህበራት እና 101 የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሰረታዊ ኀብረት ስራ ማህበራት በመረከብ ስራውን መስራት ጀመረ፡፡የአደራጅ ተቋሙ በ1988 እስከ 1993  በአሉት በጀት አመት ህብረት ስራ ማህበራትን መልሶ የማጠናከርና በአዲስ የማደራጀት ስራ በመሰራቱ በ5 የስራ መስኮች ላይ የተሰማሩ 1,065 መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት ቁጥር ሊያድግ ችሏል፡፡

በ1994 ዓ/ም አጋማሽ በተካሄደው የመ/ቤቶች አዲስ አደረጃጀት እንደገና ሲዋቀር በአዋጅ ቁጥር 6ዐ/1994 በቢሮ ደረጃ ተዋቅረው የነበሩት መምሪያዎች ቁጥር ወደ ሁለት ዝቅ ብሏል፡፡በዞንደረጃየነበረውመዋቅርደግሞሙሉበሙሉፈርሶበወረዳበግብርናስርሁኖበዴስክደረጃስራዉእንዲቀጥልተደርጓል፡፡ከዚህበመቀጠልየኅብረትሥራማህበራትንእንቅስቀሴየሚመራናየሚደግፍራሱንየቻለአላማአሰፈጸሚተቋምእንዲኖርበመታመኑበአዋጅቁጥር 124/1998 የክልሉኅብረትሥራማኅበራትማስፋፊያኤጄንሲእንዲቋቋምተደርጓል፤በወረዳደረጃምበግብርናናገጠርልማትጽ/ቤትስርበዴስክ፣በቡድንናበሥራሂደትተደራጅቶነበር፡፡እንደዚህበተለያየአግባብሲደራጅከቆየበኃላበተለይምከ2003 በጀትዓመትጀምሮበሁሉምየገጠርወረዳዎችናበ3ቱሜትሮፖሊታንከተሞችበጽ/ቤትደረጃተደራጅቶወደስራተግብቷል፤የህብረትስራተቋምከክልልእስከቀበሌራሱንችሎየሚመራበትአደረጃጀትተፈጠረለት፡፡በተዘረጋውመዋቅርአቅምበፈቀደመጠንአሰፈላጊየሰውሃይል፣ማቴሪያልናበጀትበመመደብበክልሉውስጥበዓይነት፣በቁጥር፣በካፒታልመጠንበርካታየኅብረትሥራማኅበራትእንዲቋቋሙናእንዲጠናከሩበማድረግኃላፊነቱንእየተወጣይገኛል፡፡

በአዋጅቁጥር 280/2014 ዓ.ምበአማራብሔራዊክልላዊመንግሥትየተሻሻለውየአስፈጻሚአካላትእንደገናማቋቋሚያናሥልጣንናተግባራትመወሰኛአዋጅመሰረትየአብክመኀብረትስራማህበራትማስፋፊያባለስልጣንተብሎተደራጅቷል፡፡የአደራጅተቋሙከክልልእስከቀበሌድረስ 4324 የሰውኃይልይዞእየተንቀሳቀሰይገኛል፡፡

የቅርብ ጊዜ ዜናዎች

አቅጣጫዎች

Scroll to Top